መምህር ስመኘዉ መብራቱ ካሳ

በመምህርነት ዘርፍ የ2010 ዓ.ም. የበጎ ሰው ተሸላሚ

መምህር ስመኘዉ ለታጠቅ ለስራ 1ኛ ደረጃ ትምህር ቤት እና ለአረብ ገበያ ከተማ እንዲሁም በአጠቃላይ ለታች ጋይንት ወረዳ የሰራዉ ስራ እጅግ ለትዉልድ ጠቃሚና አረአያ የሚሆኑ ነው፡፡ በወረዳዉ መልካም የሚባሉ ስራዎች ካሉ የተሰሩት በመምህር ስመኘው ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ ድጋፍ ነዉ፡፡ መምህርነትን ከልቡ የሚወድና እስካሁንም የመምህር ባህታዊ ሆኖ ተጨባጭ ለዉጦችን እያመጣ እያስተማረ፣ ትምህርት ቤቱን እየመራ፣ ትዉልድን እየቀረጸ ያለና መምህርነትን ከበጎ ተግባራት ጋር የነፍስ ጥሪዎቹ የሆኑለት ሲሆን መምህራንን ለአላማ ማስተባበር  ተማሪዎችን ማጀገን የሚችል  ታላቅ መምህር ነው፡፡

ጮራ ቤተመጻህፍት የስነ-ጥበብና  የበጎ አድራጎት ክበብ በግሉ በማቋቋም በወረዳዉ የግል ቤተ መጻህፍት ቤት ያቋቋመ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ልዩ ልዩ መጻህፍትን ከማሟላት በተጨመሪ በአንድ ጊዜ 120 ተጠቃሚዎችን ማስተናገድ የሚችል ቤተ መጻህፍት አቋቁሟል፡፡  የስነ ጥበብና የበጎ አድራጎት ክበቡ ደግሞ በወረዳዉ ለሚካሄዱ የህብረተሰብ የማንቃትና የማስተማር ስራዎች ጉልህ ሚና እየተወጣ ነው፡፡

የክረምት በጎ አድራጎት ስራችን ከዩኒቨርሲቲ የሚመለሱና በየደረጃው ያሉ ሌሎቸ ተማሪዎችን በማሰባሰብ የኪን ስራዎችንና የማስተማር ድጋፍ እንዲሰሩ በማድረግ ተማሪዎች ለላቀ ውጤት እንዲበቁ ህብረተሰቡ ደግሞ እንዲነቃ በጎ አርአያ እንዲያገኙ በየዓመቱ ነሐሴ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎችን በወረዳ ደረጃ ሽልማት እንዲያገኙ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በወረዳዉ በሚካሄዱት የታጠቅ  ለስራ ትምህር ቤት የብር ኢዩቤልዩ በዓልና ባዛር ላይ በተደረገዉ የመጽሄት ዝግጅት  ላይ በወረዳዉ ሀገራዊ ፋይዳና ጠንካራ ሰዎችን ለመዘከር የመጽሄት ሽፋን እንዲያገኙ ከማድረጉም በተጨማሪ የወረዳዉ ነዋሪዎች አርአያ ሰዎቻቸዉን እንዲያዉቁት አድርጓል፡፡

በወረዳዉ ማየት ለተሳናቸዉ ህጻናት ትምህርት ቤት ባልተከፈተበት ወቅት ከመንግስት ተሳትፎ ዉጭ በጮራ በጎ አድራጎት ክበብ በኩል ወደ ሌሎች ቦታዎች በመላክ ሙሉ ወጭ የሸፈነ በመሆኑ፡፡ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ የመንግስት ድጋፍ ሳይኖር ማየት ለተሳናቸዉ ትምህርት ቤት የከፈቱ ሲሆን ለአንድ አመት ተማሪዎች ቦታዉን እስኪለምዱና የወረዳዉ አመራር አካላት ድጋፍ እስኪያደርጉ የትምህር ቤቱ አጠቃላይ መምህራን በማስተባበር የአንድ አመት ቀለብ፣ አልባሳትና የትምህር መሳሪያዎች እንዲሟሉላቸዉ ያደረገ ሲሆን ከአንድ አመት በሁዋላ የወረዳዉ አመራር አካላት ድጋፍ መስጠት ጀምረዋል፡፡ በዘንድሮዉ አመት 10ኛ ክፍል የተፈተኑ ተማሪዎች እንዳሉ እየገለጽኩ ትምህር ቤቱም 87 ተማሪዎች ያሉት እንዲሆን በማድረጉ ነዉ፡፡

የተፈጥሮ ሃብት መንከባከብን በተመለከተ በየአመቱ ከዩኒቨርሲቲ የሚመጡ ተማሪዎችንና ሌሎች በጎ ፈቃደኞችን በማስተባር በከተማዉ በተለያዩ የመንገድ አካባቢዎችና በትምህርት ቤት ዉስጥ እንዲተከሉ የሚያደርግ ከመሆኑም በተጨማሪ በታጠቅ ትምህርት ቤት ክልል ዉስጥ 50 ሜትር በ180 ሜትር በሆነ  ልዩ ቦታ ሃገር በቀል የሆኑ የዛፍ ዝርያዎችን በመትከል ልዩ ቦታ ያዘጋጀ ሲሆን 62 የሚደርሱ ሃገር በቀል ዛፎች እንዲያድጉ አድርጓል፡፡ ለትምህርት ቤቱ ልዩ ዉበትና መማሪያ እንዲሁም ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ትልቅ ስራ ሲሆን የወረዳዉ የግብርና ጽ/ቤትም  ለማስተማሪያና ለጉብኝት እንዲጠቀሙበት የፈቀደ በመሆኑ እነዚህ ሃገር በቀል 62 የተለያዩ ዛፎች የአካባቢ ምህዳርን ከመመለስም ሆነ ተማሪዎችና የአካባቢዉ ህበረተሰብ የዛፎችን ስም ጥቅምና ባህርያት በመረዳት ተፈጥሮን እንድናዉቅ እንዲታወቅ የሚያደርግ የተፈጥሮ ተቆርቋሪ ነው፡፡

በወረዳዉም ሆነ በተለያዩ አቅራቢያ ወረዳዎች ባዛርም ሆነ ሌሎች ሰፋ ያሉ ህዝባዊ ዝግጅቶች ሲኖሩ ያለዉን ልምድ የሚያካፍል ሲሆን ብዙዎቹ ስራዎችም የእርሱ የጣት አሻራዎች ናቸዉ፡፡ መምህር ስመኘው በቤተ ክርስትያን፣ በእስልምና እንዲሁም በሽምግልና ስራዉ የሚከበርና የሚታወቅ ነው፡፡ ትምህርት ቤቱ የመንግስትን ድጋፍ ሳይጠብቅ በትምህርት ቤሮ የተቀመጡ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ያሟላ ሲሆን ለዚህም ሶስት ሙሉ ቤተ ሙከራዎች እንዲሁም ተማሪዎች ከግማሽ ቀን ወደ ሙሉ ቀን እንዲማሩ ይችሉ ዘንድ ትምህርት ቤቱ ሙሉ አቅሙን እንዲጠቀም በማድረጉ ትምህርት ቤቱን በማዘመን ማሟላት ችሏል፡፡

ርዕሰ መምህር በሆነበት ወቅት ከፍተኛ የመማሪያ ክፍሎች እጥረት ባጋጠመ ጊዜ የወረዳዉ መስተዳድርና ትምህርት ጽ/ቤት ምንም ስራ መስራት ባልቻሉበት ወቅት በራሱ ተነሳሽነት በአካባቢዉ በሚገኙ አዋሳኝ መንደሮች ባህር ዛፍ ፣ ገለባና ጉልበት ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ጋር በማስተባበር እንዲሁም የክዳን ቆርቆሮ በወረዳዉ ባለዉ ኤፍ ኤች አይ ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት በእርዳታ በመጠየቅና በማግኘት  ከ10 በላይ መማሪያ ክፍሎችን አስገንብቷል፡፡