ትውልድ አርአያ ይፈልጋል፤ ‹‹እንደ እገሌ መሆን እፈልጋለሁ›› የሚለው አርአያ፡፡ እነዚህን አርአያዎች ማግኘት የሚቻለው ደግሞ በጎ የሠሩትን ሰዎች ስናሳውቃቸውና ስናከብራቸው ነው፡፡ በተራራ ላይ ያለች መብራት ልትሠወር አይቻላትም እንዲሉ እነዚህን መብራቶች ወደ ተራራው ማውጣት ያስፈልጋል፡፡

የ 2009 ዓ.ም ሽልማት ቀጥታ ስርጭት

5ኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር ነሐሴ 28 ቀን 2009 ዓ.ም በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ይካሄዳል


የበጎ ስው ሽልማት ኮሚቴ ሰብሳቢ ሙሓዘ ጥበባት
ዳንኤል ክብረት በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል
በሰጡት መግለጫ በ 10 የሽልማት ዘርፎች 30
እጩዎችን አስታውቀዋል።

1. መንግስታዊ የሥራ ሐላፊነትን በብቃት መወጣት ዘርፍ  
 • ዶ/ር መስፍን አርአያ - ለብዙ ዓመታት የአማኑኤል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር
 • አቶ ገመቹ ዳቢሶ - ዋናው ኦዲተር
 • አቶ ማቴዎስ አስፋው - የአዲስ አበባ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር 
 2. ሚዲያና ጋዜጠኝነት
 • እሽቴ አሰፋ (ሽገር ሬድዮ)
 • ንጉሴ አክሊሉ (ለብዙ አመታት በኢትዮጵያ ሬዲዮ ያገለገለና በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋዜጠኛ)
 • ሽገር ኤፍ ኤም

   3. ማህበራዊ ጥናት

 • ኤመሪተስ ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ ( የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ፣የታሪክ መምህርና የታሪክ መጻህፍት ደራሲ)
 • ዶ/ር የራሰ ወርቅ አድማሴ (በአ/አ/ዩ የነገረ ማህበረሰብ ተመራማሪ)
 • ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ (በአ/አ/ዩ/የፓለቲካ ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር)

   4. ለኢትዮጵያ መልካም የሠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች

 • ቦብ ጌልዶፍ (በ1977 ድርቅ ወቅት ዓለም ዐቀፍ የሙዚቃ ባለሙያዎችን አስተባብሮ ለኢትዮጵያ እርዳታ የሰበሰበ)
 • ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን (የፌስቱላ ሆስፒታል መስራች)
 • ፕ/ር ጃኮብ ሽናይደር (በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚያገለግሉ የስዊዘርላንድ ሐኪም)

   5. ቅርስ፣ባህልና ቱሪዝም

 • ጉዞ አድዋ
 • አቶ ገ/ኢየሱስ ሃ/ማርያም (የጉራጌ አካባቢ ቅርሶችና ባህልን በማጥናት፣በመጠበቅና ማሰባሰብ)
 • የደ/ማርቆስ ዩንቨርስቲ

   6. ሳይንስ

 • ዶ/ር ቦጋለ ሰለሞን (የካንሰር ስፔሻሊስት)
 • ኤመሪተስ ፕ/ር ንጉሴ ተበጀ (በአ.አ.ዩ ተ/ፕ/ር)
 • ሎሬት ዶ/ር ለገሠ ወ/ዮሐንስ (የብልሐርዚያን መድሃኒት ያግኙ)

   7. ኪነጥበብ (ቴአትር ዘርፍ)

 • ተስፋዬ ገሠሠ (ታዋቂ የቴአትር ባለሙያና መምህር)
 • ጌትነት እንየው (ገጣሚ፣ተዋናይ፣ጸሃፊ ተውኔትና አዘጋጅ)
 • ዓለማየሁ ታደሰ(ተዋናይ፣አዘጋጅና፣የቴአትር መምህር)

   8. ንግድና የሥራ ፈጠራ

 • ኢ/ር ጸደቀ ይሁኔ (የፍሊንት ስቶን ባለቤት)
 • አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ (የእሽሩሩ የሥልጠና ማእከልባለቤት)
 • ሸዋ ዳቦና ዱቄት

   9. መምህርነት

 • መ/ር ፈቃደ ደጀኔ (ከ1970 ጀምሮ በመምህርነት በመርሃ ቤቴና አርሲ ያስተማሩ፣በገጠር ት/ቤት ያሰሩ፣ልጆችን እየረዱ የሚያስተምሩ)
 • መ/ር ሰለሞን ጸደቀ (በወሎቦረና፣ጋሞጎፋ፣ደ/ማርቆስ፣ወለጋ፣ጉራጌ ዞን ከ1973 ጀምሮ የሠሩ፣በገጠር ት/ቤቶችን ያሰሩ፣ ለገጠር ህዝብ የልማት ተቋማትን ያሰሩ፣ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዋችን የሚያስተምሩ)
 • አቶ ማሞ ከበደ ሽንቁጥ (የታወቁ የትምህርት ባለሙያ፣በጎልማሶች ትምህርት ላይ ለውጥ ያመጡ)

   10. በጎ አድራጎት

 • መቅደስ ዘለለው (የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት ድርጅት መስራች)
 • ዳዊት ሃይሉ (የውዳሴ ዳይግኖስቲክ ማእከል ባለቤት፣ለብዙ ችግረኞችን በነጻ ህክምና እንዲያገኙ ያስቻሉ)
 • ሰለሞን ይልማ (በደ/ዘ/ት ከተማ ችግረኞችን በመርዳት የሚታወቅ)