የ2009 ዓም የበጎ ሰው

 

ልዩ ተሸላሚ

ገና ከልጅነት እድሜያቸው ጀምሮ ለስፖርት የተፈጠሩ እንደሆኑ መናገር ይቻላል። እግር ኳስ ህይወታቸው ቢሆንም ሩጫን ይወዳሉ የብስክሌት ስፖርትንም አልፈውበታል። እድሜያቸው አስራ አራት አመት እስኪሆን ዘመናዊ የፈረንሳይኛ ትምህርትን በተለያዩ ት/ቤቶች ተምረዋል ጣልያን ኢትዮጵያን ከወረረ በኋላ ደግሞ የጣልያንኛን ትምህርት የተማሩ ሲሆን በአጠቃላይ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛና ጣልያንኛን ጨምሮ በአጠቃላይ በአምስት ቋንቋዎች ይጽፋሉ ይናገራሉ።

በተለያየ መስክ ሀገራቸውን ለማገልገል ክህሎት ቢኖራቸውም የሳቸው የህይወት ጥሪ ግን ከስፖርት ጋር ተቆራኝቶዋልና እሳቸውን ከስፖርት ውጪ ማሰብ ይከብዳል። ከልጅነት እድሜያቸው ጀምሮ የእግር ኳስ ሰው ነበሩ። ለሀያ ሶስት አመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ አምበል ሆነው በተጫዋችነት እንዲሁም በአሰልጣኝነት፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ አስራ አምስት ጨዋታዎች ላይ የተሰለፉ እና ብሔራዊ ቡድኑን ያሰለጠኑም ነበሩ። የእሳቸው የእግር ኳስ ተሳትፎ ግን ከዚህም ይሻገራል አርቢትር ሆነው አጫውተዋል፣ የእግር ኳስ ክለቦችና ፌዴሬሽኖችን አደራጅተዋል፣ የስፖርት ህጎችና ደምቦችን በአማርኛ ቋንቋ በመተርጎም አሰናድተው ለሀገራችን አስተዋውቀዋል፣ አልፎ አልፎም በሬዲዮ የእግር ኳስ ጨዋታን አስተላልፈዋል ከስፖርት ኮንፌዴሬሽን ዋና ጸሀፊነት እስከ ምክትል ምክትል ሚኒስትርነት ስፖርቱን መርተዋል። ከካፍ ፕሬዚዳንትነት እስከ የአለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባልነት አገልግለዋል።

የኢትዮጵያን እግር ኳስ እፍ ብለው ሕይወት ከዘሩበት በኋላ ወደአፍሪካ መድረክ ሄደውም ከግብጽ፣ ከሱዳን እና ከደቡብ አፍሪካ ጋር በመሆን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን እንዲመሰረት አገራችን ያበረከተችውን ጉዞ ቀይሰዋል። በጊዜው ከደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽ እና ሱዳን ጋር በመሆን አፍሪካ በታዛቢነት በተሳተፈችበት የፊፋ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አፍሪካ በፊፋ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ እንድትወከልና የራስዋ ኮንፌዴሬሽንን እንድታቋቁም ያቀረቡት ጥያቄ ከዘረኝነት በመነጨ አስተሳሰብ በጊዜው የነበሩ የአለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር /ፊፋ/ ሰዎች “እንዴት ተደርጎ?” ብለው አንቀበልም ሲሉ እሳቸው ከአፍሪካ አጋሮቻቸው ጋር በመሞገት የሶቪዬት ህብረት እና የደቡብ አሜሪካ ሀገሮችን አሳምነው ባገኙት ድጋፍ አፍሪካ የራስዋ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ሊኖራት ቻለ።

የካፍ ስራ አስፈጻሚ አመራር ላይ ከመጡ በኋላም አድሎዋዊነት የተሞላበትን እና አግባብነት የሌለውን አለም አቀፋዊ አሰራር አጥብቀው መቃወማቸውን በመቀጠል ሁለት ፌዴሬሽኖች የነበሩትን የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ማህበር በአንድ በኩል ነጮችን ብቻ የያዘ ማህበር በሌላ በኩል ደግሞ ጥቁሮችና ሌሎች ዘሮችን የያዘውን ማህበር ፍጹም ዘረኝነት የተሞላበት እንደሆነ በመግለጽ ነጮችና ጥቁሮችን ያካተተ ቡድን እስካላቋቋመች ድረስ ደቡብ አፍሪካ ከፊፋ አባልነት መታገድ አለባት በማለት አጥብቀው መከራከር ያዙ። በጊዜው የፊፋ ፕሬዚዳንት የነበሩት ስታንሊ ሮውስ ይህንን ሀሳብ አልቀበልም አሉ እሳቸው ግን በካፍ አመራርነት ኃላፊነታቸው ወደምክትል ፕሬዚዳንትነት ካደጉ በኋላም ይህንን አቋማቸውን ገፍተውበት ቶክዮ ጃፓን በተካሄደው የፊፋ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በድጋሚ የአፓርታይዷ ደቡብ አፍሪካ ከፊፋ አባልነት እንድታገድ ጠየቁ ጥያቄው ከብዙ ትግል በኋላ ተቀባይነት አገኘ።

አፍሪካ በአለም ዋንጫ ለመሳተፍ የምታልፍበት መንገድ ማለት “ግመል በመርፌ ቀዳዳ …. ” የሚባለውን አይነት ነበር ማለት ይቻላል። በጊዜው ሰላሳ አባል ሀገራት የነበሩት ካፍ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊው ከእስያ ዋንጫ አሸናፊ ጋር ተጫውቶ ያሸነፈው ብቻ በአለም ዋንጫ የሚሳተፍበት ጊዜ ነበር ይህ አልበቃ ብሎ የፊፋ አመራሮች አፍሪካ በአለም ዋንጫ ላይ ያላት ድርሻ እዚህ ግባ የሚባል ስላልሆነ በሁለት ተከታታይ የአለም ዋንጫ ወይም ኦሎምፒክ ላይ ያልተሳተፈ ፌዴሬሽን በፊፋ ስብሰባ ላይ መሳተፍም ሆነ መምረጥ አይችልም የሚለውን ሀሳብ ሲያዘጋጁ ይህንን ሀሳብ በመቃወም እንዲያውም አፍሪካ በአለም ዋንጫ እራሷ ተወካይ ሊኖራት ይገባል በማለት ሞግተው በዚህም ሞሮኮ በአለም ዋንጫ አፍሪካን የወከለች የመጀመሪያዋ ሀገር ለመሆን ቻለች።

በካሜሩን ያውንዴ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ሱዳናዊውን ዶ/ር አብዱልሃሊም መመድን በመርታት የካፍ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡ በኋላም የአፍሪካ አገራት በፊፋ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር እንደሚችሉ ጆ ቫላንጅን በማሳመን በለም ዋንጫ የሚወክልዋት ሀገራትን ቁጥር ለማሳደግ ከፍተኛ ርተዋል። የአፍሪካ የወጣቶች ዋንጫ እና የክለቦች ዋንጫ አሸናፊ ውድድሮች እንዲጀመር አድርገዋል። የካፍ ገቢን በማሳደግም በተለይም በካፍ ውድድር ከቴሌቪዥን ርጭት ከፍተኛ ገቢ እንዲገኝ አስችለዋል። ከፊፋ የሚገኘውን ገቢም እንዲያድግ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ እግር ኳስን ጨምሮ ሌሎች ስፖርቶች ላይ የሩ፣ የተጫወቱ፣ ያለጠኑ፣ በአመራርነት ያገለገሉ፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት የቻሉ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ። ካፍን በፕሬዚዳንትነት በመሩበት አራ አምስት መታት እንዲሁም በራ አስፈጻሚነት ዘመናቸው በአጠቃላይ በርካታ ራዎችን የሩ ሲሆን በተለይ ደግሞ የትንባሆና የአልኮል ማስታወቂያዎች በአፍሪካ ስቴድየሞች እንዳይሰቀሉ ማድረጋቸው፣ የደቡብ አፍሪካን የአፓርታይድ ርዐት አጥብቀው የታገሉ አፍሪካ በስፖርቱ መስክ አልጣኞች፣ ዳኞች፣ ኪሞች እና ሌሎች የራሴ የምትላቸው ባለሞያዎች እንዲኖሯት የተጉ፣ አፍሪካ በፊፋ መድረክ እንድትወከል ያደረጉ፣ በለም ዋንጫ የአፍሪካ ኮታ እንዲሻሻል የለፉ ኢትዮጵያዊ።  ከአባታቸው ባለቅኔ ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ሙላትዋ ገ/ላሴ በጅማ ከተማ የተወለዱ ሲሆን ነሴ 13 1979 ከዚህ ለም በሞት ተለይተዋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የዳጊዎችን ውድድር በስማቸው ሰይሟል፣ በቅርቡ የተመረቀውን አካዳሚ በስማቸው እንዲጠራም አድርጓል፡፡ ለሀገራችንና ለአህጉራችን ከሰሩት ራ አንጻር በተለይ በአዲሱ ትውልድ የሚታወሱበት ማስታወሻ የሚገባቸው የኢትዮጵያና የአፍሪካ ስፖርት ታላቅ ባለውለታ ናቸው።

የ2009 ዓም የዓመቱ በጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ

ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ