ዶክተር መስፍን አርአያ

መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣት ዘርፍ 2009 የበጎ ሰው ተሸላሚ

ዶክተር መስፍን አርአያ ነሐሴ 1946 አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ በሕክምና የዶክትሬት ዲግሪ (MD) ከቅዱስ ፒተርሰበርግ የሕክምና ትምህርት ቤት (ሩሲያ) 1972 .. ያገኙ ሲሆን በአእምሮ ሕክምና ስፔሻሊቲ ዲፕሎማ (DPM) ከግሮኒንገን ዩኒቬርሲቲ (ኔዘርላንድስ/ Netherlands) 1982 ተቀብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዶክተር ኦፍ ፊሎሶፊ ዲግሪ (PhD) ከኡሜዮ ዩኒቬርሲቲ (ስዊድን) 2000 .. አግኝተዋል፡፡

ዶክተር መስፍን አርአያ በተለያዩ የኃላፊነት መስኮች ሀገራቸውን ያገለገሉ ሲሆን በራስ ስብሐት ሆስፒታል፣ አዲግራት/ትግራይ (1974/75) ጠቅላላ ሐኪምና የሕክምና ዳይሬክተር፣ደሴ ሆስፒታል፣ ደሴ(1975/76) ጠቅላላ ሐኪምና የሕክምና ዳይሬክተር፣አማኑኤል የአእምሮ ሆስፒታል(1976/79) ጠቅላላ ሐኪምና የሕክምና ዳይሬክተር፣አማኑኤል የአእምሮ ሆስፒታል፣ (1982/1987) የአእምሮ ሐኪም፣ቅዱስ ጳውሎስ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ (1987/2006) የአእምሮ ሐኪምና መምህር፣በዘውዲቱና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ 1997/እስከ አሁን የአእምሮ ሐኪምና መምህር፣በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአእምሮ ሕክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ (1995/2001) የቅዱስ ጳውሎስ የሕክምና ትምህርት ቤት ዲን፣ (2001/2003) የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒዬም ሜዲካል ኮሌጅ ፕሮቮስት፣(2003/2006)፣በአዲስ አበባ ዩኒቬርሲቲ የአእምሮ ሕክምና ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር (1999/አስከ አሁን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

ዶክተር መስፍን አርአያ ለዚህ አገልግሎታቸው ከተለያዩ ተቋማት ልዩ ልዩ ዕውቅናና ሽልማቶችን አግኝተዋል፡፡ ከቴዎዶርና ቫዳ ስታንሊ ፋውንዴሽን (Theodore and Vada Stanely Foundation USA) ለከፍተኛ የአእምሮ ጤና አገልግሎት በኢትዮጵያ፣ 1992 (USA) የረጅም ጊዜ ኅብረተሰብን የማስተማርና የማገልገል አድናቆት ሰርቲፊኬቶች፣ ከራዲዮ ፋና፣ ከጤና አጠባበቅ ማህበራት፣ ከፒፕል ፒፐል (People to People, PLC), ኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር፣ ተስፋ ጎህ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ወገኖች ማኅበር፣ ከፋርሚድ፣ ወዘተ ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሮበርት ጊል (Robert Giel) ወርቅ ሜዳሊያ (የአእምሮ ጤናን ለማሻሻል ለተደረገ ተዋጽዖ) 1998 .. አግኝተዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር (የተምሳሌታዊ የሕክምና አገልግሎት ዕውቅና) 2003 .. የወርቅ ሜዳሊያ የተሰጣቸው ሲሆን ከፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር (የረጅም ጊዜ ተምሳሌታዊ የጤና አገልግሎት ዕውቅና) 2006 .. የወርቅ ሜዳሊያ ተበርክቶላቸዋል፡፡ ከምግብ መድኃኒት ቁጥጥርና አስተዳደር ዋና መሥሪያ ቤት (ተምሳሌታዊ የረጅም ጊዜ የጤና አገልግሎት) 2006 .. የወርቅ ዋንጫ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ዶክተር መስፍን አርአያ የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ጤና አጠባባቅ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ የአእምሮ ሕክምና ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አባል ሲሆኑ  የብሔራዊ ኤች አይ መከላከልና መቆጣጠር ጽሕፈት ቤት አደራጅ ግብረ ኃይል አባል፣ የብሔራዊ ኤች አይ መከላከልና መቆጣጠር ምክር ቤት መሥራች አባል፣ የተስፋ ጎሕ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ወገኖች ማኅበር የአማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ፣ የብሔራዊ ይቅርታ ቦርድ አባል፣ የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ጆርናል ዋና አዘጋጅ (Ethiopian Medical Journal Editor-in-Chief) የመድኃኒትና ሕክምና አቅራቢ ድርጅት (ፋርሚድ/PFSA) የቦርድ ሰብሳቢ፣ የአእምሮ ጤና ክብካቤ ማኅበር በኢትዮጵያ የቦርድ አባል፣ የፌዴራል ሆስፒታሎች ማኔጅመንት ቦርድ አባል፣ የአማኑኤል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ማኔጅመንት ቦርድ አባል፣ የመድኃኒትና ምግብ ቁጥጥርና አስተዳደር (FMHACA) የአማካሪ ቦርድ አባል፣ በመሆን ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

 

በእነዚህና በሌሎች ለሀገራቸው በሠሯቸው ሥራዎች ምክንያት በዳኞች ውሳኔ በ2009 ዓም መንግሥታዊ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣት ዘርፍ የዓመቱ በጎ ሰው ተሸላሚ ሆነዋል፡፡