ትውልድ አርአያ ይፈልጋል፤ ‹‹እንደ እገሌ መሆን እፈልጋለሁ›› የሚለው አርአያ፡፡ እነዚህን አርአያዎች ማግኘት የሚቻለው ደግሞ በጎ የሠሩትን ሰዎች ስናሳውቃቸውና ስናከብራቸው ነው፡፡ በተራራ ላይ ያለች መብራት ልትሠወር አይቻላትም እንዲሉ እነዚህን መብራቶች ወደ ተራራው ማውጣት ያስፈልጋል፡፡

2. በ ንግድና ስራ ፈጠራ ዘርፍ የ 2009 ዓ.ም. የበጎ ሰው ተሸላሚ

ሸዋ ዳቦና ዱቄት (አቶ ዘሙይ ተክሉ ቅስሙ)

ሸላሚ አቶ ኢየሱስወርቅ ዛፉ ከ1950ዎቹ ጀምሮ በበርካታ ሀገራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የተሳተፉ፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የመጀመሪያው ሥራ አስኪያጅ፣ የሕብረት ባንክ እና የሕብረት ኢንሹራንስ መስራች፣ በ2008 ዓ.ም በንግድና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ የበጎ ሰው እጩ ተሸላሚ። ሽልማቱን የአቶ ዘሙይ ልጅ ተቀብለዋል። የሸዋ ዳቦና ዱቄትን ሙሉ ታሪክ ያንብቡ

1. በመምህርነት ዘርፍ የ 2009 ዓ.ም. የበጎ ሰው ተሸላሚ

አቶ ማሞ ከበደ ሸንቁጥ

ሸላሚ የ 2008 ዓ.ም. በመምህርነት ዘርፍ ተሸላሚ የነበሩት አቶ አውራሪስ ተገኝ ናቸው። የአቶ ማሞ ከበደን ሙሉ ታሪክ ያንብቡ

3. በ ማህበራዊ ጥናት ዘርፍ የ 2009 ዓ.ም. የበጎ ሰው ተሸላሚ

ኤምሪተስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ

ሸላሚ ፕሮፌሰር ባዬ ይማም፣ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ስነልሳን ጥናት አንጋፋ ምሁር። የኤምሪተስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴን ሙሉ ታሪክ ያንብቡ

4. በሳይንስ ዘርፍ የ 2009 ዓ.ም. የበጎ ሰው ተሸላሚ

ኤምሪተስ ፕሮፌሰር ንጉሴ ተበጀ

ሸላሚ ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእጽዋት ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ ምሁር። የኤምሪተስ ፕሮፌሰር ንጉሴ ተበጀን ሙሉ ታሪክ ያንብቡ

5. ለኢትዮጵያ በጎ የዋሉ የውጭ ሃገር ሰዎች ዘርፍ የ 2009 ዓ.ም. የበጎ ሰው ተሸላሚ

ዶ/ር ኤሊኖር ካትሪን ሃምሊን

ሸላሚ አቶ በላይ ግርማይ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባልደረባ። የየኤሊኖር ካትሪን ሃምሊንን ሙሉ ታሪክ ያንብቡ

6. መንግስታዊ የስራ ሃላፊነትን በብቃት በመወጣት ዘርፍ የ 2009 ዓ.ም. የበጎ ሰው ተሸላሚ

ዶክተር መስፍን አርአያ

ሸላሚ አቶ ይርጋ ታደሰ፣ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ምዝገባ ጽ/ቤት በሃላፊነት የሰሩ፣ የ2006 ዓ.ም. የበጎ ሰው ሽልማት እጩ ተሸላሚ ። የየዶክተር መስፍን አርዓያን ሙሉ ታሪክ ያንብቡ

7. በቅርስና ባህል ዘርፍ የ 2009 ዓ.ም. የበጎ ሰው ተሸላሚ

    

ጉዞ አድዋ

ሸላሚ አቶ አብዲ ነጋሽ፣ ጥንታዊ መጻህፍትን በመሰብሰብና ለተጠቃሚዎች በማቅረብ የሚታወቅ ወጣት ። የጉዞ አድዋን ሙሉ ታሪክ ያንብቡ

8. በኪነ-ጥበብ/ቲአትር/ ዘርፍ የ 2009 ዓ.ም. የበጎ ሰው ተሸላሚ

    

አርቲስት ተስፋዬ ገሰሰ

ሸላሚ አርቲስት ስዩም ተፈራ፣ አንጋፋ ተዋናይና የግጥም ደራሲ ነው። በአሁኑ ሰዓት በማለዳ ኮከቦች የተዋንያን ውድድር ላይ በዳኝነት እንዲሁም ዘመን ድራማ ላይ በተዋናይነት በመስራት ላይ ይገኛል። የየአርቲስት ተስፋዬ ገሰሰን ሙሉ ታሪክ ያንብቡ

9. በጋዜጠኝነትና ሚዲያ ዘርፍ የ 2009 ዓ.ም. የበጎ ሰው ተሸላሚ

    

ጋዜጠኛ ንጉሴ አክሊሉ

ሸላሚ ወ/ሮ እሌኒ መኩሪያ፣ የሬዲዮና ቴሌቪዥንን ጋዜጠኝነት ካስተዋወቁ እንስት መካከል አንዷ ናቸው። በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ። የየጋዜጠኛ ንጉሴ አክሊሉን ሙሉ ታሪክ ያንብቡ

10. በበጎ አድራጎት ዘርፍ የ 2009 ዓ.ም. የበጎ ሰው ተሸላሚ

    

አቶ ዳዊት ሃይሉ (ውዳሴ ዳያግኖስቲክስ ሴንተር)

ሸላሚ አቶ መሃመድ ካሳ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያጋጥሙ የአደጋ ክስተቶች ወቅት ቀድመው ከሚገኙ እና አፋጣኝ ድጋፍን በማስተባበር ከሚታወቁ ወጣት ኢትዮጵያውያን ተጠቃሽ። የየአቶ ዳዊት ሃይሉ (ውዳሴ ዳያግኖስቲክስ ሴንተርን) ሙሉ ታሪክ ያንብቡ

11. የ 2009 ዓ.ም. የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ

              

ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ

ሸላሚ ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ፣ ኢትዮጵያን ከ5000 ሜትር እስከ ማራቶን ድረስ ባሉት ርቀቶች ባለ ታሪክ ያደረጋት ብርቅዬ ልጅ፣ 27 የዓለም ክብረወሰኖችን የሰባበረ፣ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች፣ ለብዙዎች የስራ እድል የፈጠረ ባለሃብት፣ የኒውዮርክና ለንደን ማራቶን አማካሪ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት። የየክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማን ሙሉ ታሪክ ያንብቡ

5ኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር ነሐሴ 28 ቀን 2009 ዓ.ም በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ይካሄዳል


የበጎ ስው ሽልማት ኮሚቴ ሰብሳቢ ሙሓዘ ጥበባት
ዳንኤል ክብረት በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል
በሰጡት መግለጫ በ 10 የሽልማት ዘርፎች 30
እጩዎችን አስታውቀዋል። ሙሉ ዝርዝርሩን ያንብቡ